image
image
image
image
image

በብልፅግና ፓርቲ የልደታ ክፍለ ከተማ ቅ/ፅ/ቤት ለአመራርና አባላት ዳታቤዝ አደረጃጀት፣ የመረጃ አያያዝ እና የዲጂታል መታወቂያ ህትመትን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫና ሙያዊ ስልጠና ተሰጠ።

መስከረም 14, 2019
የስልጠናው ዋና ዓላማ የመረጃ ጥራትንና ትክክለኛነትን ማረጋገጥ፣ መረጃን በቀላሉ ተደራሽ ማድረግ፣ ተቋማዊ አሰራርን ማጠናከር፣ አሰራርን ማዘመንና ማቀላጠፍ እንዲሁም አደረጃጀቱን ብቁና በቴክኖሎጂ የታገዘ የሰው ሃይል ማስደገፍ ነው። የልደታ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደረጀ ትሪቦ በሰጡት ሀሳብ፣ በየደረጃው የሚዘጋጁ መረጃዎች ትክክለኛ፣ ወቅታዊና በጥራት የተደራጁ መሆን እንዳለባቸው ገልጸው፤ የአመራርና አባላት ዳታቤዝን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ማድረግ ለተቋማዊ አሰራር፣ ለተጠያቂነትና ለአሰራር ቅልጥፍና ወሳኝ መሆኑን አሳስበዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት አይሲቲ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሲሳይ ጥላሁን በሙያዊ ስልጠናውም ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ሥርዓት በመዘርጋት የተደራጀና ቀልጣፋ አሰራር መፍጠር፣ የመረጃ ጥራትን ማሻሻል እና የዲጂታል መታወቂያ ህትመት ሥራን በተቀናጀ መልኩ ማከናወን በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ገለጻ ተደርጓል። በተጨማሪም በየደረጃው ያሉ የዘርፉ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የመፈጸም አቅማቸውን በማሳደግ፣ የመረጃ ሥርዓቱን በተገቢው ሁኔታ በመተግበር ተቋማዊ አሰራርን በማጠናከር ረገድ የሚጠበቅባቸው ኃላፊነት ተጠቁሟል። በመጨረሻም የተሰጠውን ስልጠና በፍጥነት ወደ ተግባር በመቀየር፣ የመረጃ ጥራትን በማረጋገጥና የዳታቤዝ አደረጃጀቱን በማጠናከር የፓርቲውን ውስጣዊ አሰራር የሚያዘምንና የሚያሳድግ የመረጃ ሥርዓት በቁርጠኝነትና በተጠያቂነት ስሜት መተግበር እንደሚገባ ተገልጿል።

መልዕክትዎን ይላኩ