image
image
image
image
image

የሀገራችን ድምቀትና የአለም ቅርስ ከሆኑ የአደባባይ በዓላት አንዱ የሆነው የመስቀል ደመራ በዓል በሁሉም ባለዶርሻዎች ትብብር በአዲስ አበባ ከተማ በየዓመቱ በከፍተኛ ድምቀት ኦየተከበረ እንደሚገኝ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።

መስከረም 17, 2019
በ2019 የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ከንቲባ አዳነች የከተማችን ድምቀት ከሆኑ የአደባባይ በአላት አንዱ የሆነው የመስቀል ደመራ በዓል፡ለዘመናት ሐይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ፡በባህላችን ደምቆ ሲከበር የኖረ ታላቅ በአል ነው ብለዋል፡፡ የመስቀል በዓል መሠረት በይቅርታና በፍቅር የመሻገር መሆኑን ያስታወሱት ከንቲባ አዳነች በዓሉን ስናከብር በፍቅርና ይቅርታ በዓሉ ያለውን ተምሳሌትነት እያሰብን ሊሆን እርስ በእርስ በመዋደድ እና በመከባበር እንንዲሁም በመደጋገፍ ሊሆን ይገባል ብለዋል። የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ ሲከበር በርካታ ዘመን ተሻጋሪ ሁለንተናዊ ፋይዳዎችንአ ቅፎይ ይዛል ያሉት ከንቲባ አዳነች በዓሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኔስኮ (UNESCO) በይፋተመዝግቦ የሰው ልጅ የጋራ ማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ በመሆን በዓለም ሀገራዊ ገፅታችንንና የባህል ሃብታችንን ከፍ ያደረገ እሴታችን ነው ሲሉም ገልጸዋል። በደመራው ዙሪያ የሚበሩት በርካታ ነጠላ ችቦዎች እያንዳንዳቸው የየራሳቸው ብርሃን ያላቸው ፤ ነገር ግን ሁሉም በአንድነት ተሰብስበው ወደ ደመራው ሲቀላቀሉ አካባቢውን በሙሉ የሚያደምቅ፣ጨለማውን የሚገፍና አቅጣጫን የሚያሳይ ታላቅ የጋራ ብርሃን ይፈጥራሉያሉት ከንቲባ አዳነች።ይህም የእርስ-በርሳችን የተጋመደ አንድነታችን ከዚህ ተምሳሌት ጋርአ ንድነት እንዳለው ማሳያ ነው ብለዋል። የተለያየ ባህል፣ ቋንቋና ማንነት ቢኖረንም፣ እንደ ደመራው በጋራ ስንቆም፣እጅለእጅ ተያይዘን ስንራመድና ህብረታችንን ስናጠናክር ለከተማችንና ለሀገራችን የማይበገር ታላቅ ብርሃንና ጥንካሬእ ንሆናለን ሲሉም ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ደመራው የሚያስተላልፍልን ዋናው መልእክትም አብሮነት፣ህብረትና አንድነት ሁልጊዜም ጥንካሬ ፈጥሮ ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሆን ነው። ያሉት ከንቲባዋ ከተማችን አዲስአበባ፣ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የዓለም የስህበት ማዕከል፣የንፅህና ተምሳሌት፣ በአጭር ጊዜ የተከናወነ የከተማለ ውጥአብነት ሆናለች፡፡ በዚህች ውብ፣ ፅዱ እና ለመኖርምቹ የሆነች ከተማችንን፣ በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችንና ዓለማቀፍ እንግዶችን በታላ ቅስነ-ስርዓትና በብቃት እያስተናገደች ነው፡፡ከተማችን ታላላቅ ሀገር-አቀፍና ዓለም-አቀፍ ኹነቶችንና እንዲሁም ሀገራዊ የአደባባይ በአላትን በስኬትየመምራት፣ የማስተናገድ አቅሟ በከ ፍተኛ ደረጃማ ደጉን ለዓለም እያስመሰከረችነው ብለዋል፡፡ ለመላው የከተማዋና የሀገራችን ነዋሪዎችም መልካም የደራ እና የመስቀል በዓል እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። #lideta_prosperity

መልዕክትዎን ይላኩ