image
image
image
image
image

መደመር የሚጎለብተው በአብሮነት፣ በመረዳዳትና በበጎነት ነው!

መስከረም 15, 2019
የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት የኢትዮጵያዊ አብሮነት፣ የወንድማማችነት፣ የፍቅርና የመረዳዳት እሴቶችን የምናጎለብትባቸው የጋራ የደስታ ወቅቶች ናቸው። ከመደመር እሳቤ አንፃር የጋራ እሴቶቻችንን ማጠናከር በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባርም መገለጥ ይገባዋል። በጎ ፈቃድ፣ እንግዳ ተቀባይነት፣ መረዳዳትና ለሌላው ደህንነት መቆም የመደመር ተግባራዊ መገለጫዎች ናቸው። ብልፅግና እሳቤ ደግሞ የሁሉንም ዜጎች ተሳትፎ፣ የጋራ ኃላፊነትና የጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ አብሮ የመልማት እሳቤን ያጎላል። ስለዚህ በዓላቱ በሰላም፣ በፍቅርና በደስታ እንዲከበሩ እያንዳንዳችን የድርሻችንን መወጣት ይገባናል። ከተለያዩ አቅጣጫዎች የምንመጣ ብንሆንም፣ በኢትዮጵያዊ አብሮነት አንድ ነን፤ በመደመር አስተሳሰብ የጋራ ነገዳችንን እንገነባለን። #lideta_prosperity

መልዕክትዎን ይላኩ